ኦሮባ  (WELCOME)

ኢሮብ ማለት/ስንል

ABOUT IROB PEOPLE

 ኢሮብ በአሁኗ ትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምስራቅ የምትገኝ ወረዳ ናት የኢሮብ ማዕከልና ለረጅም ዓመታት ዋና ከተማ የነበረችው 'ዓሊቴና' ከክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ 155 ኪሜ የምስራቃዊ ዞባ ዋና ከተማ ከሆነችው ዓዲግራት ደግሞ 45 ኪሜ ርቀት ላይ ትገኛለች ኢሮብ ላለፉት 28 ዓመታት "በልዩ ወረዳነት" ስትመደብ የወቅቱ ዋና ከተማ ደግሞ "ዳውሓን" ትባላለች ዳውሓን' ለዓሊቴና ቅርብ ስለሆነች ከዓዲግራት  ተመሳሳይ ርቀት ላይ ትገኛለች እጅግ አነስተኛ በሆነ የመሬት ስፋት ላይ ያረፈችው 'ዳውሓን' የወደፊት ዕድገት የተወሰነ እንደሚሆን ከወዲሁ ይገመታል

የኢሮብ የመሬት መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ/ቶፖግራፊ/ እጅግ ተራራማና ቀጥ ባሉ ሸንተረሮችና ጥልቅ (deep) ሸለቆዎች የተሞላ ነው በዚህም የተነሳ ታራሽ መሬቱ እጅግ አነስተኛ ሲሆን ከአጠቃላይ ይዞታው 1% እንደማይበልጥ የሚጠቁሙ ጥናቶች አሉ። የአከባቢው የአየር ሁኔታ ደረቃማ(arid) ሲሆን ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም አነስተኛ የሚባል ነው።

 ኢሮብ፣- በምዕራብ አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪ ሕዝቦች ጋር የምትዋሰን ሲሆን፣ ይህንን ምዕራባዊ መስመር ይዘን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ስንጓዝ ኢሮብ በጉሉማክዳ ወረዳ ስትዋሰን፣ ቀሪው ደግሞ በኤርትራው የአካለ-ጉዛይ ትግርኛ ተናጋሪ አጎራባች ሕዝብ ትዋሰናለች። ቀጥሎ ያለው ሰሜናዊ ጫፍ ደግም ከአምባ ሶይራና ማኮ ከሚባሉ የኤርትራ የመሬት ይዞታ እና ሴሚናዊ የኢሮብ ጫፍ የመሬት ይዞታ መኻል ሰንጥቆ ወደ ዒንደሊ በሚወርደው ወንዝ ትዋሰናለች። አሁንም ይህን ወንዝ ሳንለቅ ተከትለን ከሰሜን ጫፍ የምስራቁን አቅጣጫ ይዘን ወደ ደቡባዊ ጫፍ እስክንደርስ ደግሞ በኤርትራዊያን የሳሆ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ጋር ትዋሰናለች። ዙረን ወደ ደቡባዊው ጫፍ ስንመለስ ደግሞ በዓፋር ክልልና ከሳዕሲዕ-ፃዕዳእምባ ወረዳ ጋር ትዋሰናለች። 

የኢሮብ ምስራቃዊ ወሰን ራንዳ-ኮማ እና ራጋይሊ ድረስ ስለሚዘልቅ እስከ ቀይ ባሕር የሚተርፈው የየብስ ርቀት ሩቅ ኣይደለም።

በሌላ አነጋገር ከየትኛውም የትግራይ መሬት እንደ ኢሮብ ለቀይ ባሕር የቀረበ ቦታ የለም። የኢሮብ ሕዝብ ከነዚህ አጎራባች ሕዝቦች በሰላም በመከባበርና በፍጹም መግባባት የኖረና የሚኖር ሕዝብ ነው። ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ ትስስሩም የተሳሰረና የተጋመደ ነው። "ኢሮብ' ሲባል የማሕበረሰቡና የወረዳው የጋራ ስያሜ የሚወክል ሲሆን፣ ወረዳ = ኢሮብ ማሕበረሰብ = ኢሮብ በመባል ይታወቃል። ቋንቋውም 'ሳሆ' ይባላል። የኢሮብ ሕዝብ የራሱ ወግ፣ ባህልና እሴቶች እንዲሁም የራሱ የሆነ የፓለቲካ-እሳቤና የግንባታ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው። አዋሳኝ ትግርኛ ተናጋሪ ሕዝቦች አከባቢውን "ዓዲ-ኢሮብበማለት ሲጠሩት ነዋሪውን ደግሞ "ሕዝቢ-ኢሮብ" ይሉታል።  ሳሆ ተናጋሪዎች ሕዝቡን 'ኢሮብ' መሬቱን ደግሞ 'ኢሮብ-ዲክ/ኢሮብ-ባዶ' በማለት ሲጠሩት፣ የሁለትዮሽ ማሕበራዊ ትስስሩን "ኢሮብከ-ሓዶ" በሚል ሲገልጹት ኢሮቦችም በተመሳሳይ ሓዶከ-ኢሮብ በማለት የተለየ ቅርበትና ሚዛን ይሰጡታል።

 

የኢሮብ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሲሆን እጅግ አነስተኛ መጠን ያላቸው የእስልምና ተከታይ ነዋሪዎችም ይገኛሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አብዛኞቹ ሰዎች የኢሮብ ሕዝብ የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ብቻ እንደሆነ ይገምታሉ። ግምቱ ግን የግንዛቤ ክፍተት ከመሆኑ ውጭ መሬት ላይ ያለ ሃቅ አይወክልም። ይልቁንም ከኢሮብ ሕዝብ የካቶሊክ ተከታዩ 1/3 ገደማ ብቻ ሲሆን አብላጫው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው። የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኣከባቢዉ ከሁሉም የቀደመ ረጂም ዕድሜ አለው። በመቀጠል ደግሞ ኢሮብ ህዝብ የደቂቀ ኢስጢፋኖስ ተከታዮችን በመቀበልና በማስተናድ ይታወቃል። ሁለቱንም፣ ማለት የቆየው የኦርቶዶክስ-ተዋህዶ እምነት ተከታዮችንና ደቂቀ ኢስጢፋኖስችን ጎን ለጎን አስተናግዷል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ዝነኛው የጉንዳጉንደ ገዳም የሚገኘው በኢሮብ ወረዳ ሲሆን፤ ለግዞተኞች የደቂቀ ኢስጢፋኖስ መነኮሳት መጠግያ እንዲሆናቸው የኢሮብ ህዝብን በማስተባበር ጉንዳጉንዴን ያስገነባው ቡራሱባጋዲስ የሚባሉ የሓሳባላ-ኢሮብ ተወላጅ ናቸው። ገዳሟ የተገነባችው ዓሲምባ ተራራ ግርጌ ስር ካለው ሰዋራ ቦታ ሲሆን፤ ሽሽት ላይ ለነበሩ መነኮሳት እጅግ አመቺ ሆናላቸዋለች። የደጃች ሱባጋዲስ አስከሬንም በኑዛዜያቸው መሠረት ወደ ትውልድ ቦታቸው እንዲመለስ ሆኖ በዚችው ገዳም ተቀብሯል። ኣሁንም የደጃች ሱባጋዲስ አስከሬንና የሁለት ልጆቻቸው (የደጃች ወልደሚካኤልና የደጃች ሓጎስ) ሬሳዎች የያዙ ሳጥኖች በገዳሙ ቅጥር ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ።

በተመሳሳይ በሰሜኑ ያገራችን ክፍል የካቶሊክ እምነትን ተቀብሎ በማስተናገድ አሁንም የኢሮብ ሕዝብ ቀዳሚ ነው። ቀጥሎም መነሻውን ዓሊቴና በማድረግ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ተስፋፍቶ ኤርትራን ቀጥሎም ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎችን እንደአዳረሰ ይታወቃል።

የኢሮብ ሕዝብ እንግዳን በመቀበልና በማቀብ የሚመስለው የለም። ኢሮቦች ዘንድ ሰውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ሽምጋይም ሽምግልናም የማይገኝለት ክሕደት ነው። ከዚህ ጥፋት ውጭ ሽማግሌና ሽምግልና የማይፈታው ወንጀል የለም።

ሌላውና የኢሮብ ሕዝብ አስመልክቶ ብዙዎችን ሲያወዛግብ የሚታየው ጉዳይ ቢኖር የኢሮብ ሕዝብ ልክ እንደ ዓፋርና ኩናማ በኤርትራና በኢትዮጲያ ውስጥ ይካለላል ወይም ይኖራል የሚል ሲሆን፣ መልሱ ግን አጭርና ግልፅ ሆኖ የኢሮብ ሕዝብ የሚገኘው ኢትዮጲያ ትግራይ ውስጥ ብቻ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን የኢሮብ ሕዝብ በመዋዕሉ ኤርትራ ውስጥ የተካለለበት ወይም የተዳደረበት አንዳች ወቅት አልነበረም፣ ኖሮም አያውቅም። እንዲያውም እንደ እውነቱ ከሆነ ዘመናዊ የአከላለል ስርዓት ተጀምሮ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በራሱ አካባቢና የአስተዳደር ስርዓት፣ ማንነቱን ጠብቆ የኖረ ሕዝብ ነው። የራሱ ሕግጋት በማርቀቅ ልክ እንደ ዘመኑ ቃለ ጉባኤ ያዥ በመሰየምና በየርዕሱ የሚይዙ ሰዎች በመሰየም በሕግ አግባብ ሲተዳደር ነበር። (ለምሳሌ፤ ቃለጉባኤ ለመያዝ የተለየ የማስታወስ ተሰጥዎ ያላቸው ሶሰት ሰዎች የሚመረጡ ሲሆን የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ብዥታ ሲፈጠር እነዚህ ሰዎች ይጠሩ ነበር ይባላል) ይህ ብቻ ሳይሆን በአግባቡ ስላልተሰነደ ነው እንጂ ሌላውን የአከባቢ ሕዝቦችን ከዘመናዊ ሕግጋት ጋር ያስተዋወቀ ሕዝብ ነው።

አሁንም ከኢሮብ ጋር ተያይዞ መረሳት የሌለበት ሌላ ጉዳይ ቢኖር የትምህርት ጉዳይ ነው። ይኸውም መደበኛ ትምህርት ኢሮብ ዓሊቴና ውስጥ የተጀመረው 1830ዎቹ መጨረሻ አከባቢ ሆኖ ይህም በሀገሪቱ ደረጃ ቀዳሚ ያደርገዋል። ለዚህ ደግሞ የካቶሊክ ቤተ/ያን ግዙፍ አስተዋጽኦ የሚረሳ አይደለም።


ኢሮብ አድቮካሲ አሶሴሽን

ታሕሣሥ 01/2015

Though the website contains general information about Irob in many sections, we thought providing a brief introduction about Irob from the outset could be helpful.

----

By Sauba Hais

Most of the three Irob groups claim to be descendants of one man, Summe. Acccording to the oral history of the people and several written records, Summe’s father, Negus (King) Werede-Mehret, is believed to have come from Tsira'e in Kilite-Awla'elo, Tigray about 800 years ago. That is around the time when the so-called “Salomonic” dynasty took control of political power of the Ethiopian empire from the Zagwe dynasty. It is recounted that WoredeMehret, himself a local king, was a descendant of Emperor Yitbarek of the Zagwe dynasty. Negus WeredeMehret’s forefathers left their ancestral land probably for political reasons related to the change of political power in Ethiopia. In fact, for many centuries, the Irobs isolated themselves to this remote, militarily strategic, mountainous region keeping their distance from the political centers.

Many different tribes inhabited the Irobland before the descendants of Weredemehret went there. But most of those tribes left the region for good. The main ethnic group who dwelled in the region when the descendants of Weredemehret moved there were the Kayayta people. Today too the Kayayta people are one of the main social groups who live in the Irobland. The Aydola (Aydoli-dik) are some of the early inhabitants of the region as well. Anyway it is not the purpose of this article to deal with the question of the Irob ethnic group in general. However, putting it briefly the Irob ethnic group is a community composed of the descendants of Kayayta, Summe, Aydola, Ga’aso, Dabrimela, Hado/Hazo and some few members of other lineages.

Most of the Irobs may be descendants of the Zague Dynasty, the Lasta kings. Hence it is interesting to know that the Irob oral history narrates that, when the Ethiopian political center moved from Shewa to Gonder, some Irob leaders such as Ona Tensa’e and Ona Kumanit (Some say his son Tesfahanis) traveled to Gonder likely to get a firsthand account of what was happening and may had been to establish some type of relationship. It is recounted that the two men returned with “Gamma,” a traditional symbol of the blessing of the Emperors, demonstrating that the local authority of the individual who received the 'Gamma' had been approved.

When the descendants of Summe got to the new land, they brought with them the Christian religion, which they have kept to date. It seems that the people who inhabited the region were Christians as well. Because there are many ruins of churches apparently predated the epoch the new comers arrived. Anyway it is recounted that Summe built a new church in a locality called Halalisse near his first permanent settlement. The place where he built his first home is called Harare-Ababena and the locality where he built the church is just a stone’s throw from the first residence. They dedicated the church to St. Mary and they named it Kidane-Mehret (Covenant of Perpetual Mercy). The local residents still call the site Summae Massoare (the Church of Summe). It is said that they gave the name Tsira'e to the mountain overlooking the site of the first permanent settlement in the memory of their ancestral land.  Go here to read the entire article

Copy of IAA fact sheet amharic version.pdf

IAA's VISION

ራእይ

The vision Irob Advocacy Association is to realize a socio-economically empowered vibrant Irob, where all democratic rights are fully observed. IAA envisions an Irob society that is aware of its rights, history, culture, and social values and norms, and strives to preserve them and its identity.

ጠንካራ ማሕበረ-ቁጠባዊ መሰረት ዘለዎ፤ ሰብዓዊን ዴሞክራሲያዊን መሰላት ዝተሓለወሉን ዝተማለአሉን፣ ብዲሞክራሲያዊ ኣተሓሳስባ ዝማዕበለ፣ ብመንነቱ ዝሕበን፣ ኣብ ዝነብረሉ ከባቢ ኩሉ ኢሮባዊ፣ ስነልቦናን ሓድነቱን ዝሓለወ ህዝቢ ኢሮብ ምርኣይ እዩ። 

MISSION

ተልእኾ

Our mission is to bring Irob unity and empowerment and also forge strong partnerships with like minded organizations and people that promote democracy and minority rights. To conduct studies and research to discover opportunities for sustainable development, avert threats by creating awareness and recommending preventive measures. Thus, IAA shall work so that the safety and security of Irob people is guaranteed. Strive for the emergence and flourishing of a united Irob with strong socio economic and democratic foundations utilizing all advocacy avenues advocacy tools like organizing, lobbying, educating, and litigation when deemed necessary.

ናይ ኢአአ ተልእኾ ውሽጣዊ ሓድነት ህዝቢ ኢሮብ ብምጥንኻር፤ ምስ ካልኦት መሰል ትካላትን ህዝብታትን ናይ ዕላማ ሓድነትን ምትሕብባርን ብምፍጣርን ብምዕቃብን፣ ናይ ህዝቢ ኢሮብ ህልውናን ድሕንነትን ብምሕላውን ንኽሕሎ ብምግባርን፣ ቀፃሊ ዕድላትን ውሕስናን እቲ ህዝቢ ብመፅናዕቲን ምርምርን ብምድጋፍ፤ ቀፃልነትን ህልውናን ብሀረሰብ ኢሮብ ብዝለዓለ ብርኪ ምርግጋፅን  ክቕፅል  ምግባርን እዩ። 

Values

ክብሪታት ኢ.ኣ.ኣ  

Under any circumstances prioritize people's needs to effectively tackle major issues of Irob people, despite the needs and priorities of individual or a group.


Ensure transparency by conducting the day to day businesses in an ethical, accountable and trust worthy behavior and according to the bylaws of the organization and standards to fulfil the the goals and mission as set forth.


Our organization, its leaders and staff as well as our supporters makes sure that services are delivered to our people free of discrimination due to their differences in regions of residence, age, religion, gender, clan or alliance/affiliation to any groups.


Embrace differences in opinions and views of individuals and groups by cultivating a culture of civilized discourse and negotiations skills and settlement of disputes and disagreements by majority rule when differences are obvious. Respect majority vote and democratic decisions even when major disagreements arise.


Cultivate a culture of cooperation and collaboration with all regional, national, and international groups who respect and support the good will and ambitions of IAA and the Irob public.


ኣብ ዝኾነ ይኹን ግዜን ኩነታትን ካብ ናይ ውልቃዊን ጉጁላዊ ስምዕትን ድሌትን ናይ ህዝቢ ውራይ ብምቅዳም እቶም ኣውራ ናይ ህልውናና ፈተናታት(ብዲሆታት) ዝኾኑ ፀገማት ኹሉመዳያዊ ልምዓታት ከከም ኣድላይነቶምን ቀደምሰዓቦምን ኽቃለሉ ምስራሕ፣


እንሰርሖም ስራሓውቲ ኣብ ዕላማታት ቃልሲ ሕገ ደምቢ መታሓዳደሪ ሰነድ ብዘሰፈረን ሕጊ ብዝፈቅዶን መሠረት ብግልፀኝነት፣ ተሓታትነት፣ ተኣማንነትን ፅቡቅ ስነ-ምግባርን ብምስራሕ ሓላፊነት ምውፃእ፣ 


ኩሎም ኣመራሪሓን ኣባላትን ድርጅት ከምኡ እውን ሓገዝትናን ብሓፈሻ ኩሉ ህዝብና ብዘይ ምንም ዓይነት ናይ ኣካባቢ፣ ቋንቋ፣ ኃይማኖትን፣ ፆታ፣ ዓሌት('ሜላ')፣ ኣረኣእያ ፖለቲካ፣ ብርኪ ትምህርቲ፣ ዕድመን ወዘተ ኣፈላላይን ወገናውነት ነፃ ብዝኾነ ንኹሎም ብማዓርነት ምሰራሕ፣ 


ናይ ሰብ ኣፈላላይ ሓሳብን ኣረኣእያን ብምኽባር፣ ምድምማፅን ምዕቡል ባህሊ ምይይጥን ክሪክሪን ብምዕባይ ብምክያትን መርትዖን ምእማን (ምትእምማን)፤ ስፍሕ ዝበሉ ናይ ሓሳብ ኣፈላላያት ወይ ዘይምሪዲዳእ እንትፊጠሩ ብሓበራዊ ምይይጥ ምፍታሕ፣ ሓበራዊ ዋኒን ብምቅዳም ውሳነ ኣብዛሓ ብፀጋ ናይምቅባል ባህሊ ምንጋስ፣


ምስ ህዝብና፣ ኣብ ኣከባብና፣ ኣብ ውሽጥ ዞባና ይኹን ክልል ዝነብሩ ይኹን ኻልኦት ጎረባብቲን ኣሕዋት ህዝብታትን፣ ምስ ኩሎም ሃገራውን ዓለምለኻዊ ደገፍቲ ልምዓት ህዝቢና ሓውስካ ምስ ኩሎም ዝምልከቶም ብምርድዳእን ሓዲነትን ብምስራሕ ርኡይ ለውጥ ምምሕያሽ ብምምፃእ ረብሓን ተጠቃሚነትን ህዝብና ምርግጋፅን። 

What Prompted THE NEED FOR Advocacy?

ኢሮብ  አድቮኬሲ  አሶሴሽን  ንኽጣየሽ  ቀጥታ  ምክንያት ዝኾኑ ነገራት

Disclaimer

This website has been established by Irob Advocacy Association (IAA) to house knowledge products and information about IAA, research articles, facts, and information about Irob minority. Stay tuned for new updates and check our site regularly to learn more about Irob and IAA.

IAA dedicates the website to the Irob heroes and heroines who paid the ultimate sacrifices to defend Irob people and their homeland, those who stand with truth and justice, past and present.