Updates

ቢቢሲ ከመቀሌ ነዋሪዎች አገኘሁ ባለው መረጃ

መጋቢት 27፣ 2014 ዓ/ም


✔ በከተማዋ መቶ ኪሎ   ጤፍ ከ 7,040 ብር ላይ ሆኗል።

✔አንድ ሌትር ነዳጅ አስከ 100 ብር ድረስ ይሸጣል።

✔ለአንድ ጉዞ  የባጃጅ ተሳፋሪዎች   እስከ 100 ብር ድረስ ያወጣሉ

✔ የመኪና ግዢ ፍላጎት እጅግ ስለቀነሰ 800, 000 ብር ሲሸጡ የነበሩ መኪኖች በ350,000 ብር ድረስ እየተሸጡ ነው ።

✔24 ካራት የጣት ቀለበት ወርቅ ከ 3,200 ብር በላይ ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን በከተማዋ ከ620 ብር በታች እየተሸጠ ነው ።

✔ትራንስፖርት ውድ ስለሆነ በከተማዋ ሳይክል የሚነዳ ሰው በዝቷል። በዚህም ምክንያት የብስክሌት ዋጋ በጣም ጨምሯል።

ህይወት በመቀሌ!

❤ አንድ የመቀሌ ነዋራ የሆኑ አባት ከBBC አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ይላሉ።

"በየቀኑ በህይወት ለመኖር የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት ከፍተኛ ጭንቀት አለው የሁለት ትንንሽ ልጆች አባት እንደመሆኔ ለቤተሰቤ የሚያስፈልገውን ሁሉ አለማሟላቴ ልቤን ሰብሮታል ባንኮች ስለተዘጉ ያለኝን ገንዘብ አውጥቼ መጠቀም ባለመቻሌ ምንም ማድረግ አልቻልኩም እኔ ብቻ ሳልሆን በርካታ ነዋሪዎች ይህንኑ ፈተና እየተጋፈጡ ነው ከፍተኛ የገንዘብ እጥረትም አለ ከባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ አካውንቴ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ማውጣት ባለመቻሌ ከጓደኞች እና ዘመዶች ብር እየተበደርኩ ለቤተሰቤ ምግብ ለመግዛት ተገድጃለሁ።

✍️ በውጭ ሃገር ያሉ ዘመዶቻችን መርዳት ቢፈልጉም የቴሌኮም አገልግሎቶች ስልክና ኢንተርኔት በመቋረጣቸው ይህንንም እርዳታ ልናገኝ አልቻልንም ይባስ ብሎ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ንሯል ዋነኛ ምግብ የሆነውን ጤፍ፣ የስንዴ ዱቄት፣በርበሬና ዘይት ዋጋ የማይቀመስ ሆኗል ከአመት በፊት 100 ኪሎግራም ጤፍ ወደ 4 ሺህ 200 ብር ገደማ ይሸጥ ነበር፤ በአሁኑ ወቅት ግን 7 ሺህ 600 ብር እየተሸጠ ነው አቅሙ ያላቸው አነስተኛ መጠን ያለው ጤፍ ገዝተው ከማሽላና ስንዴ ዱቁት ጋር በመቀላቀል እንጀራ ይጋግራሉ። ሆኖም ለበርካታ ነዋሪዎች ጤፍ መግዛት የማይታሰብ ነው።"

"በትግራይ ለምግብነት የማይውሉ የነበሩ ፍራፍሬዎች መንገድ ላይ እየተሸጡ ይገኛሉ በየግቢያችን አትክልት እንድንተክል ተነግሮን እነሱንን እየኮተኮትንና እያሳደግን ነበር። ችግሩ ግን ውሃ ማግኘት አልቻልንም። ቀደም ብሎ ለሳምንት የሚሆን 200 ሊትር የሚይዘውን በርሜል እንገዛ ነበር በአሁኑ ወቅት ግን እሱን ለመግዛት አቅሙ የለንም።

❤ስለዚህ ውሃ የምናመጣው ጥልቀት ከሌላቸው ጉድጓዶች እየቀዳን ነው።ለልጆች አዲስ ጫማ፣ ልብስ መግዛት እና ስጋ መብላት ቅንጦት ሆኗል። በመቀለ የውሃ እና የመብራት አገልግሎት የተገደበ ነው፤ ቀኑን ሙሉ ሲመጣና ሲጠፋ ነው የሚውለው። አንዳንድ ጊዜም ያው መብራት ሳናገኝ ቀናቶችን እናስቆጥራለን። በርካታ ነዋሪ እየሰራ አይደለም፤ ከስራ ውጭ ሆኗል። በርካታ ሱቆችና የንግድ ማዕከላትም ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው ወይም የሚሸጡት እቃዎች በማጣታቸው ተዘግተዋል። እነዚህን መከራዎች ለመወጣት ነዋሪዎች እንደ መኪና፣ የቤት እቃዎች እና ጌጣጌጦችን በኪሳራ ለመሸጥ ተገድደዋል። ከእነዝህ ብዙዎቹ ልጆች የያዙ እናቶች ናቸው። የጤና ማዕከላትም መድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች አልቆባቸዋል።"

"ስር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ህመምተኞች በመድኃኒት እጦት ምክንያት እየሞቱ ነው። የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ያለባቸው ነዋሪዎች ደግሞ የጸረ ኤች አይቪ መድኃኒቶችን የሚያገኙት አንዳንድ ጊዜ ነው። በትግራይ ዘንድ ይከበሩ የነበሩና የማህበረሰቡ መገለጫ የሆኑት ሃይማኖታዊ በዓላት፣ ሰርግና ሌሎች ድግሶች የሩቅ ጊዜ ትዝታ ሆነዋል። በየቀኑ ምን አደርጋለሁ? ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት አምሽቼ ነበር የምተኛው። ማታ፣ ማታ መሰብሰብ የቻልኳቸው ዜናዎች በሙሉ አዳምጣለሁ፤ ቪዲዮዎችንም አያለሁ። በቅርብ ቀናት የተከሰቱ ዜናዎችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው።"

"የኢንተርኔት አገልግሎት ስለሌለ ይልቁንም ቪዲዮዎችንና በድምፅ የተቀዱ ዜናዎችን የሚሸጡ ሱቆች ጋር እሄዳለሁ። እያንዳንዱን ቅጅ ወደ 10 ብር ገደማ ይሸጡታል። ሌላ ጊዜ ደግሞ መፅሃፎችን አነባለሁ፣ ከጎረቤቶቼ ጋር እጫወታለሁ ወይም በእግሬ እራመዳለሁ። በመኪና መንቀሳቀስ አይታሰብም። አንድ ሊትር ቤንዚን ከጦርነቱ በፊት በነዳጅ ማደያዎች 22 ብር ይሸጥ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በሊትር 515 ብር እየተሸጠ ይገኛል። በርካቶች ብስክሌት መጠቀም ቢጀምሩም ነገር ግን ብስክሌቶች በከፍተኛ ሁኔታ ተወድደዋል። እዚህ ያለው ህዝብ ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ይፈልጋል እናም ባለፈው ሳምንት የተኩስ አቁሙን ስንሰማ በጣም ተደስተን ነበር።ሆኖም መሬት ላይ ባለው ኑሯችን ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም፤ ምንም እንኳን የእርዳታ ጭነት መኪኖች ወደ ክልሉ እየመጡ ነው ቢባልም። ባንኮች ገና አልተከፈቱም አንዳንዶችም ተኩስ አቁም "ባዶ ቃል" ነበር በሚል እየተበሳጩ ይገኛሉ። በህይወት በመቆየቴና ታሪኬን ለናንተ በማካፈሌ ደስተኛ ነኝ፤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በርካቶች ከኔ በከፋ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉና አንዳንዶቹም እየሞቱም እንደሆነ አውቃለሁ። ምናልባት ከዚህ ሁሉ በጎ ነገር መጠቀስ የሚገባው የህዝቡ እርስ በርስ መደጋገፍና መረዳዳት ነው። "ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል" የሚል አባባል አለ እናም ነዋሪው ይህንን አባባል አጥብቆ ይዟል። ነገ እንደሚራቡ እንኳን ቢያውቁትም ማህበረሰቡ ያለውን ተካፍሎ ነው የሚበላው። አብረን ለመትረፍም ተባብረን ቆመናል።"

 

"እርሱ ያውቅልናል ልጄ! ደህና_ሁን!"

ሰላም ለኢትዮጵያ