About Irob

Table of Content

Gunda Gunde Manuscripts

Some Facts About Irob

By Suba Hais Oct. 25, 1998

Irob is one of the Ethiopian territories invaded by the Eritrean armed forces this year. When news of the invasion broke, I observed that many Ethiopians, including Tigrayans, did not know anything about Irob, even its existence. After almost five months, there is not much change in this regard. The aim of this paper, therefore, is to provide some information about the people and the location. It will also discuss the current condition of the people after the invasion.

LOCATION, LANGUAGE AND RELIGION

The Irob people occupy a small, semi-arid, mountainous region with a wide altitudinal range in which almost all types of crops can be potentially cultivated. It is located in Agame, northeast Tigray/Ethiopia. The territory is bordered by the Endeli River to the east and to the north-east, by Shumezana to the north-west, by Guolomakeda to the west, Sae`se` to the south and Afar Region to the south-east. The Irob neighbors to the east and north-east are predominantly Muslims and speak the Saho language. The Afars are Muslims as well and, of course, they speak the Afar language which is very similar to the Saho language. The other neighbors are Tigrigna speaking Christian highlanders.

The Irobs who live in this geographic location speak Saho. Many other Irob descendants who live in the rest of Agame and some other adjacent places have adopted the Tigrigna language. Irob is an ethnic community made up of three sub-groups: Adgadi-ârere, Bouknaiyti-âre and Hasaballa. Adgadi-âre and Hasaballa are predominantly Tewahido Christians, while Buknaiyti-âre is mostly Catholic.

BACKGROUND

Most of the three Irob groups claim to be descendants of one man, Summe. Acccording to the oral history of the people and several written records, Summe’s father, Negus (King) Werede-Mehret, is believed to have come from Tsira'e in Kilite-Awla'elo, Tigray about 800 years ago. That is around the time when the so-called “Salomonic” dynasty took control of political power of the Ethiopian empire from the Zagwe dynasty. It is recounted that WoredeMehret, himself a local king, was a descendant of Emperor Yitbarek of the Zagwe dynasty. Negus WeredeMehret’s forefathers left their ancestral land probably for political reasons related to the change of political power in Ethiopia. In fact, for many centuries, the Irobs isolated themselves to this remote, militarily strategic, mountainous region keeping their distance from the political centers.

Many different tribes inhabited the Irobland before the descendants of Weredemehret went there. But most of those tribes left the region for good. The main ethnic group who dwelled in the region when the descendants of Weredemehret moved there were the Kayayta people. Today too the Kayayta people are one of the main social groups who live in the Irobland. The Aydola (Aydoli-dik) are some of the early inhabitants of the region as well. Anyway it is not the purpose of this article to deal with the question of the Irob ethnic group in general. However, putting it briefly the Irob ethnic group is a community composed of the descendants of Kayayta, Summe, Aydola, Ga’aso, Dabrimela, Hado/Hazo and some few members of other lineages.

Most of the Irobs may be descendants of the Zague Dynasty, the Lasta kings. Hence it is interesting to know that the Irob oral history narrates that, when the Ethiopian political center moved from Shewa to Gonder, some Irob leaders such as Ona Tensa’e and Ona Kumanit (Some say his son Tesfahanis) traveled to Gonder likely to get a firsthand account of what was happening and may had been to establish some type of relationship. It is recounted that the two men returned with “Gamma,” a traditional symbol of the blessing of the Emperors, demonstrating that the local authority of the individual who received the 'Gamma' had been approved.

When the descendants of Summe got to the new land, they brought with them the Christian religion, which they have kept to date. It seems that the people who inhabited the region were Christians as well. Because there are many ruins of churches apparently predated the epoch the new comers arrived. Anyway it is recounted that Summe built a new church in a locality called Halalisse near his first permanent settlement. The place where he built his first home is called Harare-Ababena and the locality where he built the church is just a stone’s throw from the first residence. They dedicated the church to St. Mary and they named it Kidane-Mehret (Covenant of Perpetual Mercy). The local residents still call the site Summae Massoare (the Church of Summe). It is said that they gave the name Tsira'e to the mountain overlooking the site of the first permanent settlement in the memory of their ancestral land.

At that time the Irobland was unexploited and fertile. Hence they enjoyed a comfortable life for centuries. Their economy was based on agriculture and pasturing. Not only then, until few decades ago, Irobland was a source of the best quality of honey, livestock and dairy products that used to dominate the regional markets. During the last four decades or so, because of drought and other man made factors, the region rapidly became one of the poorest spots. The problem is rooted mainly in the ecological and environmental conditions. Deforestation is almost complete in this mountainous region. The rare rainfalls, which usually come in the form of sudden heavy downpours, the irregularities of the surfaces and centuries of poor farming practices have combined to facilitate the erosion and depletion of the soil. The rainfalls and floods have carved much of the topography, changing it into rows of hollows and hills. The gravel, sand and topsoil have been washed away, exposing the bedrock to the surface in many parts. Besides the degradation of the terrain, the holdings of cultivated land per household are very small and unproductive.

From this brief description of the land one can easily visualize the condition of Irob farmers. During the last few decades the people farmed by terracing the hillsides. The land needs continuous maintenance so that it is not swept away by eventual sudden downpours. Now that the farmers are dislocated from their villages because of the Eritrean invasion, the hard work of terracing or maintaining the hillside lands has been aborted. This year's unusually heavy rains have compounded the problem.

ስለ ኢሮብ ህዝብ ታሪክ ያልተመለሱ ጥያቄዎች

ኃይለስላሴ ዮሓንስ (ሞደይሳ) , 2007 GC

መግቢያ                               

ኢሮብ በሰሜን ምስረቅ ኢትዮዽያ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞባ የሚገኝና ከኤርትራ ጋር የሚዋሰን አናሳ ብሄረሰብ የሚጠራበት ስም ነዉ፡፡ ይህ ስም በዉስጡ ቡክናይቲዓረ፡ ሓሳባላዓረንና አድጋዲዓረ የተባሉና ከአንድ የዘር ግንድ የወጡ ህዝቦችን ያጠቃልላል። ህዝቡም በጥቅሉ አዶሓ ኢሮብ /ሶስቱ ኢሮብ/ ተብሎ ሲጠራ ኖሯል። የኢሮብ አፈታሪክ አዋቂዎች ከአበው የተረከቡት የህዝቡ ታሪክ በአፈታሪክ ለትውልድ ሲያስተላለፉ ቆይቷል።

አንዳንዶቹ የኢሮብ አፈታሪክ አዋቂዎች፤ ለምሳሌ አቶ ሚካኤል ገብራይ ማይዳ ጸበቦ፣ ስለ አዶሓ ኢሮብ አሰያየም ሰፋ ያለ ትንተና ይሰጡ ነበር። በሳቸው አባባል በቀደምት ጊዜ፤ በዋናነት፣ አዶሓ ኢሮብ /ሶስቱ ኢሮብ/ ተብሎ ይጠሩ የነበሩት በአሁኗ የኢሮብ ምድር የሚገኙና ሱመ የወለዳቸው፤ በከፊል ሰራየና አከለጉዛይ የሚገኙ ሰንበታይ የወለዳቸው፤ ኢንዲሁም በጽራዕና ወምበርታ የሚገኙ ሓንናከ የወለዳቸው ሶስትየዎሽ ናቸው እንጂ በአሁኗ የኢሮብ ምድር የሚገኙ የሱመ ልጆች ብቻ አለነበሩም። እነዚህ ሶስቱ ወንድማማቾች የወለዱአቸው የወረደምሕረት የልጅ ልጆች ደግሞ በየወቅቱ በሚጠራው የነገዳቸው ሸንጎ፤ በአሁኑ አጠራር ማይ - ጻዕዳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ይሰበሰቡ እንደነበር ይተርኩ ነበር። የዚህ እውነታ፣ የኢሮብ ታሪክ በባለሙያ የታሪክ ተመራማሪዎች፤ በሳይንሳዊ ዘዴ ይጠና ዘንድ መንግሰትና የኢሮብ ህዝብ በአንድነት የታሪክ ጠበብቶች በማሰማራት የኢሮብ ህዝብ ታሪክ ኢንዲጠና ሲያደርጉ የሚታወቅ ሆኖ ለአሁኑ ግን፣ በዚህ ጽሑፍ፣ ሲነገሩ የቆዩትን የተለያዩ አባባሎች ሳይሸራረፉ ለማቅረብ እሞክራሎህ።   

በጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ ሲገለጽ፤ የኢሮብ ህዝብ በሰሜን ምስራቅ በኩል ከሳሆ ብሄረሰብ፤ በሰሜን ምዕራብና በምዕራብ ከትግራይ ብሄረሰብ እንዲሁም በደቡብና በምስራቅ በኩል ደግሞ ከአፋር ብሄረሰብ ይዋሰናል።

ከዚህ በላይ እንደጦቀምኩት፣ ስለኢሮብ ህዝብ ታሪክ የተደረገ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ባለመኖሩ ይህን ቀጥሎ የማቀርበው ጽሁፍ ምንጭ በአካል ያነጋገርኳቸው የኢሮብ ታላለቅ የአፈታርክ አዋቂዎችና ሁለቱ ስለ ኢሮብ ታሪክ በትግርኛ ተጽፈው የሚገኙ መጻህፍት ናቸው። አንቱታን ካተረፉት የኢሮብ ታሪክ አወቂዎች ውስጥ አንዳንዶቹ፤

ሀ. ከቡክናይቲዓረ፤ አቶ ዓዶዑማር ጎዕስን፤ አቶ ሚካኤል ገብራይ ሓውኩ፤ አቶ ሀይሉ ወልዱ ሞሲ ኮማን፤ አቶ ሐጎስ ማሳ ሓነይታን፤ አቶ ዳባሳይ ካህሳይ (ጎይላ) ና ሌሎቹም ሲሆኑ

ለ. ከሓሳባላዓረ፤ ባይሳይ ስበሓት እና ልጃቸው አቶ ሱባጋድስ ከሰረክለ (ዳታ አራዕ)

ሐ. ከአድጋዲዓረ ደግሞ ያባ ጊደይ ሓጎስ (ጊደይ ኡንዱዐ) የተባሉ የታሪክ አዋቂወችን ናቸው።

ሳይሳካ የቀረ የመጀመርያው የኢሮብ ታሪክ ጥናታዊ ኮንፈረንስ

እነዚህ ከዚህ በላይ ስማቸው የተዘረዘሩት የአፈታሪክ አዋቂዎች በ1974/1976 ስለኢሮብ ታሪክ የሚነጋገር አንድ የኢሮብ ተወላጆች ኮንፈረንስ በዓሊተና ለማካሄድ በተደረገው ዕቅድ፤በወቅቱ በሕይወት የነበሩት፣ በኮንፈረንሱ እንዲሳተፉና የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ የመጀመርያ ቦታ ከተቸራቸው አንዳንዶቹ ነበሩ።

በዚያን ጊዜ፣ ለኮንፈረንሱ መሳካት የብዙ ሰው በጎ ፍላጎት የተንጸባረቀ ከመሆኑ ባሻገር እያንዳንዱ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ የዓሊተና ነዋሪ በነፍስወከፍ ብር 50 ለማዋጣትም ተዘጋጅቶ ነበር።ይህን የተቀደሰ ሃሳብ ተግባራዊ እንዲሆን በግንባር ቀደመትነት የተሰለፈው የዓሊተና ልደታ ለማርያም መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመምህራን ቡድን ሲሆኑ ከዓሊተና ገዳም ደግሞ አባ አለማ ጊደይና አባ ፉሱሕ በረሀ የሃሳቡ ቋሚ ምሰሶ ነበሩ። አባ ሓጎስ ገብሩም ምክርና ሃሳብ በመስጠት ተሳታፊ ነበሩ።ሲስተር ዘወይ የተባሉና በወቅቱ በዓሊተና “የዶተርስ ኦፍ ቻሪቲ” (Daughters of Charity) የተባለ በጎ አድራጊ ድርጅት ሥራ አስከያጅ የነበሩ ደግና አስተዋይ ሓላፊ ደግሞ ለኮንፈረንሱ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸው አረጋግጠው ነበር። ሆኖም ግን በወቅቱ አከባቢያው፤ ግፈኛውን የደርግ ሥርዓት ለመጣል ይካሄድ የነበረውን የትግራይ ህዝብ ትግል ይመራ በነበረው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት ቁጥጥር ሥር በመኖሩና ከደርግ ወታደረዊ የጦር ኃይል ጋር በመፋለም ላይ ስለነበረ፤በሁለቱ መሃከል ይካሄድ በነበረው ጦረነትና አለመረጋጋት ምክንያት ለውጤት ሳይበቃ ቀረ።

ጉዳዩ እንዲህ ነው። በተለይ በቡክናየቲዓረ ”ህዝቢ - ክፍሊ” ሆኖ የአስተዳደር ጉዳዮችን እንዲከታተል ተመድቦ ይሠራ የነበረው አስፍሓ የተባለ ደግና አስተዋይ እንዲሁም ትዕግሰተኛ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት ታጋይና ተወካይ ኮንፈረንሱን ለማካሄድ ጥያቄ ሲቀረብለት ጉዳዩን ለበላይ አሳውቆ ከተነጋገረበት በኋላ መልስ እንደሚሰጠን ነገረን። መልስ ማግኘቱ ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም የተገኘው ምላሽም ቢሆን ፈታኝ ነበር። መልሱም፣ ኮንፈረንሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት ታዛቢዎች ወይም ተወካዮች በተገኙበት ማካሄድ እንደሚንችል ሲያበስር የኮንፍረንሱ ውጤት ወይም ማጠቃለያ ሃሳብ ደግሞ በትግርኛ ተጨምቆ ኢንዲዘገብ የሚል ነበር።ለኮንፍረንሱ አዘጋጀቹም ሆነ ሃሳቡን ለሚደግፉ ወገኖች ግን የተሰጠው መልስ ፈታኝ ነበረ። ምክንያቱም በዚሁ ኮንፈረንስ ጦስ በትምህርት ቤቱ አስተዳደርና አባላት እንዲሁም በብዙ ድካምና አስተዋይ ልቦና የተገነባውና ለመላው የኢሮብ ህዝብ የብርሃን ጮራ የሆነው፤ኢንዲሁም በብዙ መስዋእትነት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን በሚተገብረው ታሪካዊው የልደታ ለማርያም ትምህርት ቤት ላይ፤ አፋኙ የደርግ ሥርዓት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት ታዛቢዎች ወይም ተወከዮች በኮንፍረንሱ መሳተፍ ምክንያት አድርጎ ሊያደርስ ለሚችለው ጥቃት ላለማጋለጥ ኮንፈረንሱን ላለማካሄድ ተወሰነ። በዚህም ምክንያት ከፍተኛውንና የመጀመርያውን የኢሮብ ህዝብ ታሪክ ኮንፈረንስ የማዘጋጀት ጥረት የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። ምክንያቱም የህዝብ ክፍል የነበረው ታጋይ አስፍሃም፤ የድርጅቱ ውሳኔም ቢሆን የማይቀለበስ መሆኑን ደግሞ ስላስረገጠ ነበር።

ያልታቀደ የኢሮብ ታሪክ ሰሚናር

የመጀመረያው የኢሮብ ታሪክ ሰሚናር ተግባራዊ የሆነው በኢትዮዽያ ርእሰ ከተማ በአድስ አበባ በ1984/85 ዓ.ም በካቶሊካዊት ቤተክርሰትያን ካቴድራል የምእመናን አደራሽ ነበር። በሴሚናሩም ሶስት ጽሁፎች ቀርበው ነበር።

ለሰሚናሩ መነሻ ሃሳብ የሆነው ዋናው ምክኒያት በወርሓ ግንቦት 1983 ዓ.ም የደርግ ሥርዓትን አሽቀንጥሮ የጣለው የኢትዮዽያ ኅዝባዊ ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢኅአዴግ/ የክልል መስተዳድርን ሲያዋቅርና፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦችን ሲተነትን ትግራዋይንና፤ኩናማን፤ በትክክል በስማቸው አስፍሮ ሲያበቃ፤ የኢሮብ ብሄረሰብን ግን የሳሆ ብሄረሰብ ብሎ በመሰየሙ ነበር።

በወቅቱ ከፍተኛ የሃሳብ መንሸራሸር የታየበት መለስተኛ ውዝግብ የኢሮብ ልጆችን ለሁለት ጎራ ከፍሎ ነበር። የሃሳብ ልዩነቱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በመውጣቱ ለመላው የጋዜጣው አንባቢ ኢትዮዽያዊም ተዳርሷል። አንዱ ወገን የኢሮብ ብሄረሰብ መጠሪያ ሳሆ መሆን አለበት ብሎ ሲጽፍ ሌላው ወገን ደግሞ የኢሮብ ብሄረሰብ መጠሪያ ኢሮብ መሆን አለበት በማለት የክርክር ጭብጡን ሲቀልም ነበር። በአዲስ አበባና ዙርያው ነዋሪ ከነበሩት ውስጥ፤ እኛ ኢሮብ ስለሆን መጠርያችን ኢሮብ መባል አለበት ብሎ ይከራከር የነበረው ክፍል፣ ድመጽ ወይም ስሜት በግንባር ቀደምትነት ይስተጋባ የነበረው በተከበሩ በአቶ ኃይለሥላሴ ገብራይ ነበር። ሌላኛው ወገን ግን በጋዜጣው ላይ በሰጠው የሃሳብ ክርክር የብዕር ስም በመጠቀሙ ምክንያት ራሱን ግልጽ ሳያደርግ ነበር እምነቱን ያንጸባርቀው።

በዚያን ሂደት፣ የዝህ የብሄረሰቡ የስም ስያሜ ጉዳይ፣ ጊዜና አጋጣሚ ያገኘ የኢሮብ ተወላጅን በሙሉ በያለበት ቦታ ያነጋገረ ነበር።ውይይቱም፣ በመቀሌ፣ በዓዲግራትና፣ በኢሮብ ምድር ሁሉ በስፋት ተካሄደ።

በዝህ ውዝግብ መነሻ ምክንያትም፣ በአዲስ አበባ ይኖሩ የነበሩ አብዛኞቹ የኢሮብ ተወላጆች በተገኙበት በተከሄደ ሰሚናር ሶስት ጽሁፎች ቀርበው ነበር። የጽሁፎቹ አቀራቢዎችም፤

1.   አቶ ኃይለስላሴ ገበራይ / የብላታ ገብራይ ወልደሥላሴ ልጅ/

2.   ዶክተር ተስፋይ ኃይለማርያም /ቀያፋ/

3.   አቶ ተስፋማርያም በረሀ /ሓሊቦ/

ከዚህ በመቀጠልም፤ ይህ ጽሁፍ የእነዚህ ሱስቱ ጽሁፎች ሃተታ፤ ዋናዎቹ የአገርቤቶቹ የኢሮብ የአፈታሪክ አዋቂዎች ከሚሉት ጋር በማገናዘብ ያቀርባል።በጥቅሉ አንኳር አንኳር ሃሳቦቹን ለመጥቀስ ያህል፤

አቶ ኃይለሥለሥላሴ ገብራይ፤ የኢሮብ ታሪክን፤ አብዛኖቹ ቀደምት የኢሮብ አበው እንደሚተነትኑት ሁሉ፤ በክብረ - ነገሥት ላይ ሰፍሮ ከሚገኘው ታሪክ፣ ማለት የኢትዮዽያ ንግስት የነበረችው ንግስተ ሳባ ንጉሥ ሰለሞንን ከመጎብኘት አፈ ታሪክ ጋር በማያያዝ መተንተኑን ተያያዙት። ከዝያም ንግሥት ሳባ ከንጉሥ ሰለሞን ጸንሳ ስትመለስ፣ ማይበላ በተባለው ወንዝ ዳረቻ የወለደችውን ቀዳማዊ ሚኒሊክ አባቱን ለመጎብኘት ሄዶ ብዙ የሚነገርለትን ታቦተ ጸዮን (The ark of the covenant) ይዞ ሲመለስ፤ ከሱ ጋር አብሮት ከመጡት መሃል ውስጥ፣ የንጉሥ መግድር እና የንጉሥ ሰለሞን እኅት የሆነችው የንግሥት ኢሌኒ ልጅ የሆነው የልዑል እስክንድር ዘር ናቸው ኢሮቦች በማለት ነበር መሠረቱን ያስቀመጡት። በመቀጠልም የልዑል እስክንድር ማረፊያ ጽራዕ ወምበርታ ተብሎ በሚጠራው የትግራይ ክልል በምሥራቃዊ ዞባ፣ በክልተ አውላዕሎ፣ በአጉላዕና አከባቢው ባለው ሰፊ መሬት እንደነበረ በመጥቀስ የእኝህ የልዑል እስክንድር የዘር ዘር የሆነው ወረደምሕረት፤ ሰንበታይ ሓንናከ እና ሱመ የተባሉትን ሶሰት ልጆቹን ይዞ አሁን የኢሮብ ልጆች ሰፍረውባት ወደምትገኘው ምድር ስላደረገው ጉዞ አብራሩ። በመጨረሻም ሱመ የአሁኑ ሶስቱ ኢሮቦች ያፈራ ሲሆን፤ ሓንናከ ወደ ትውልድ ቀዮው ተመልሶ አሁን በጽራዕ ወምበርታ በአጉላዕና አከባቢ ለሚኖረውን ህዝብ አባት ለመሆን መብቃቱን በመግለጽ ሰንበታይ ደግሞ በዛሬይቷ ኤርትራ በአክለጉዛይና በሰራየ የሚገኙትን ህዝበች በከፊልም ቢሆን ያፈራ መሆኑን የሚያስረዳ ትንተና አቀረቡ። ይህም አባባል በይዘቱ፤ አባ ተስፋስላሴ መድህን (1993)፤ ታሪኽ ኢሮብ / ሓጺር መግለጺ፤ በአማርኛ ሲተረጎም ደግሞ፤ የኢሮብ ታሪክ/አጭር መግለጫ /፤ (ትርጉም የኔ ነው) ከሚለው እና መምህር በርሀ ዝግታ (2000)፤ መበቖልን ታሪኽን ህዝቢ ኢሮብ፤ በአማሪኛ ሲቶረጎም ደግሞ፤ የኢሮብ ህዝብ ታሪክና መሰረት፤ (ትርጉም የኔ ነው)፣ ከሚለው ጋር የማይራራቅ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።  

ዶክተር ተስፋይ ኃይለማርያም /ቀያፋ/ ኢትዮዽያን ቀደም ብለው የዳሰሱና ስለ አደረጉት ጉዞና ስለ አካበቱት እውቀት በጽሁፍ የዘገቡትን የጣሊያንና የሌሎችም አገሮች ጸሓፍትና መጻሕፍት በማጣቀስ የኢሮብ ታሪክ መሰረቱ የደንከል ህዝብ መሆኑን ሲያትቱ አዳራሹ ውስጥ የነበረው የኢሮብ ተወላጅ በመገረም ነበር የተከታተለው። ስለ ዶክተሩ አንድ እውነታ መታወስ ያለበት ቢኖር፣ በኢትዮዽያ ብሄረሰብ ኢንስቲቲዩት ይሠሩ በነበሩበት ወቅት፣ በኢሮብ ታሪክ ምርምር ላይ ጊዜ ሰጥተው ሲደክሙበት የኖሩ ምሁር መሆናቸውን ነው። በአንድ ወቅት ብዛት ያላቸው ልዩ ልዩ የኢሮብ ዓዳር /ግጥሞች/ አሰባስበውና በጽሁፍ አስፍሮ ለህትመት ለማብቃት በዝግጅት ላይ እንዳሉ አስተያየቴን እንዳሰፍርበት ጠይቀውኝ በእኔ በኩል እጹብ ድንቅ መሆኑን በመግለጽ ከልቤ አድንቄላቸው ነበር። ጽሑፉ ለኅትመት ስለመብቃቱና አለመብቃቱ ግን ለማወቅ አልቻልኩም።

በዶክተሩ የኢሮብ ታሪክ አዘጋገብ ዋናው ፍሬ ሃሳብን በተመለከተ ግን፤ ማለት በወቅቱ ስለኢሮብ ታሪክ አመጣጥ የሰጡት ትንተና፣ ለብዙወቻችን የኢሮብ ተወላጆች አዲስ ነበር። የዶክተር ተስፋይ(ቀያፋ) የምርምር ውጤት የሆነውና የኢሮቦች ከደንከል ህዝብ መፍለቅ የሚገልጽ ታሪክ መቀበሉ ዳገት ነበር የሆነብን። የለም፣ እንዲህ ነው ብለን ለመከራከር ግን በጥናት ላይ የተሞረከዘ የታሪክ ጭብጥ ማቅረብ ስላልቻልን ደግሞ ዝምታውን ለመምረጥ ተገደን ጭጭ አልን።

ሶስተኛው ወረቀት ያቀረቡት አቶ ተስፈማርያም በርሀ (ሃሊቦ) ስለ ኢሮብ ህዝብ ታሪክ መሠረት ሲገልጹ የሃሳብ ክርክሩን የቆረቆሩት፤ የአሁኑ ኢሮብ ብሄረሰብ ተወላጆች በአንድ ወቀት ትግራያዊያን ነበሩ በሚል ንድፈ ሃሳብ ላይ ነበር። በአቶ ተስፋማርያም አባባል ወረደምሕረትና ልጆቹ ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ ከቀድሞ መኖርያቸው ከጽራዕ ወምበርታ ወደ ዛሬይቱ የኢሮብ ምድር እንደመጡ አቶ ኃይለሥላሴ ገብራይ ከአቀረቡት ከአብላጫው የኢሮብ ህዝብ እምነት ጋር አንድ ሲሆን፤ በእሳቸው አባባል፤

ወረደምሕረትና ልጆቹ ወደ ዛሬይቱ የኢሮብ ምድር ሲሰደዱ ቀድመውም ትግሪኛ ተነጋሪዎች ነበሩ። በቦታው ላይ ሲደርሱ ላገኙአቸው በአከባቢው ይኖሩ ለነበሩት ሳሆ ተናጋሪዎች፤ ይህ አገር ምን ይባላል? ብለው ሲጠይቁዋቸውም፤ ነዋሪዎቹ፣ እንደልማዳቸው፣ ለእንግዳ ሁሉ መልካም አቀባበል ሲሉ ሲገልጹ እንደቆዩት ሁሉ፤ ”ኦሮባ” /እንኳን በደህና መጣቹህ/ በማለት መልስ ሰጡአቸው። ወረደምሕረትና ልጆቹም ለጠየቁት ጥያቄ መልስ ያገኙ መስሎአቸዉ፤ ማለት የሳሆ ቋንቋ ካለመረዳት፤ አከባቢውን ኢሮብ ራሳቸውንም የኢሮብ ምድር ነዋሪዎች እንደሆኑ ተቀበሉ። በዚያውም ቀስ በቀስ ሳሆ ተናገሪ ትግራያዊያን ሆኑ። ስለሆነም የዛሬ ኢሮቦች የትናንትና ትግራያዊያን ናቸው፤

በማለት ለታዳሚው ጭራሽ አዲስ የኢሮብ ህዝብ ታሪክ አስደመጡ። ተሰብሳቢውም በመገረም የሚለውን አጣ።

የአቶ ተስፋማርያም የኢሮብ ታሪክ ትንታኔ ቀድሞአቸው ከቀረቡት ሁለቱ ጥናቶች የሚለይበት ዓይነተኛ ነገር ቢኖር ግን ለማመሳከርያ የሚጠቅሱት ክብረ - ነገሥት፤ መጸሓፍ፤ ወይም ሰው አለመኖሩን ነው። ይሁን እንጂ እንደ መላምት ግን፤ አቶ ተስፋማርያም ያቀረቡትን ትንታኔም ቢሆን፣ ውድቅ ለማድርግ ቀላል አለመሆኑንና፤ ስለሆነም የኢሮብ ታሪክ በቅጡ በባለሙያዎች መጠናት እንዳለበት ታዳሚው ሁሉ በዓይነ - ኀሊናው ተስማማ።

ይሁን እንጂ አንጋፋዎቹ የኢሮብ አፈታሪክ አዋቂዎች፤ ለምሳሌ አቶ ሚካኤል ገብራይ ማይዳጸበቦ እና አቶ ጊደይ ሃጎስ (ኡንዱዐ)፤ የአቶ ተስፋማርያምን አባባል ከሥረ - መሠረቱ የሚጻረር የኢሮብ ታሪክ ትንታኔ ይሰጡ ነበር። መላው ዓጋመ፣ ጉለማካዳ፣ ሳባያ፣ መኖኽሶይቶ፣ ሽመዛና፣ ናዱወ ወዘተ በእነሱ ዕድሜ፤ በከፊልም ቢሆን ወይም አልፎ አልፎ በየቦታው ኢሮብ /ሳሆ/ ተናገሪ ይገኝ እንደነበረ ምስክርነታቸውን ሰጥተውኛል። በእነዚህ የኢሮብ አፈ ታሪከ አዋቂዎች አባባል በአሁኑ ጊዜ ያ ሁሉ አልፎ ተርፎ የኢሮብ አንኳር የነበሩት እነ ማድዓና ካረዳኣ እንዲሁም ማይጺዓ፤ ኢሮብነታቸው በትግራዋይ ቋንቋና ባህል ተደፍጥጦ ይገኛል ሲሉ የሃሳብ ክርክራቸውንም ያቀርቡ ነበር። ስለሆነም የታሪክ ምስክረነት የሚያሳየው የኢሮብ - ሳሆ ተናጋሪ ህዝብ ይሸፍነው የነበረው የቆዳ ስፋት ከጊዜ ወደ ገዜ እሳት እንደነካው ላስቲክ እየተኮማተረ ወደ እጅ መዳፍ ወደምታክል ወረዳ መጨፈልቁን ነው። በዚህ ዙርያ፣ በቀጣይነት ሰፊ የአከባቢው ዕውቀት ያላቸው ተመራማሪዎችና ጸሓፍት አንዳንድ ጠቀሚ ዕውቀት እንደሚያካፍሉን እምነቴ ነው።

እለይ እንደተገለጸው የአዲስ አበባው ሰሚናር የተካሄደው በእቅድ ሳይሆን በወቅቱ ለኢሮብ ህዝብ የተሰጠና ህዝቡ የማያምንበትና የማይስማማበት አዲስ የስም ስያሜ ምክንያት ነበር፤ የሳሆ ብሄረሰብ ብሎ መሰየም። በዝህም ምክንያት፤ከላይ በዝርዝር እንዳመላከትኩት የኢሮብ ተወላጆች ጩኸት በያለበት በረከተና በረታ። መንግስትም እግዝአብሄር ይስጠውና የህዝቡን ጩኸት ሰማ። የብሄረሰቡ መጠሪያም ከጥንት ከጥዋቱ እንደቆየው እንደበፊቱ ኢሮብ ብሄረሰብ ተብሎ እንዲጠራ ሲል መንግሥት ማህተሙን አሰፈረበት። የኢሮብ ህዝብም ስሙ ስለተከበረለት ደስ አለው።

ታዲያ ያልተመለሱ ጥያቄች ምንና ምን ናቸው?

ስለ ኢሮብ ህዝብ ታሪክ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እጅግ ብዙ ናቸው። ምክንያቱም የተመለሰ ጥያቄ የለምና። ስለሆነም፣ ከዚህ በላይ ከቀረቡት ሶስት ጽሑፎች ውስጥ እንኳ የቱ ነው እውነቱ? ብለን ብንጠይቅ፤ መልሱን ለማግኘት ቀላል አለመሆኑ ግልጽ ነው። ለምሳሌ፤ አንደኛ፣ ኢሮቦች ሳሆ ተናጋሪ ትግራያዊያን ናቸውን? እንዴት? ሁለተኛ፤ኢሮቦች እውነት ከደንከል የፈለሱ ናቸውን? አይደሉም ካልን አለመሆናቸውን እንዴት እናመሳክራለን? አዎ ናቸው ብንልሳ? በመጨረሻም፣ ኢሮቦች የወረደምሕረት ልጆች፣ ብሎም የሱመ ልጆች ናቸው፤ የሚለውን መላምት እንኳ ብንቀበል፣ እንዲሁም በዛሬይቷ የኢሮብ ምድር ሱመ ከመምጣቱ በፊት፣ ቢያንስ ካያይታ የተባለ የራሱ ንጉሥ የነበረው ኃይለኛ ነገድ ነበረ ካልን (አባ ትስፋስላሴ መድህን 1993 እና መምህር በርሀ ዝግታ፣ 2000) እንዴት በዚች የአሁኗ የኢሮብ ምድር የሚገኘው ትውልድ ኢሮብ ብቻ ሊሆን ይችላል? ምክንያቱም የሱመ ልጆች ተባዝተው በዙ እንኳ ቢባል ቢያንስ ከነባሩ የአከባቢው ህዝብ ጋር በመዋሃድና በመዋለድ መሆን የለባቸውንምን ወይስ ለብቻቸው?

ከዚህም በተጨማሪ በኢሮብ ምድር ከካያይታ በፊት ይኖሩ የነበሩ ነገዶች ወይም ህዝቦች፡ ለምሳሌ እንደነ ዶባዓ፣ ኡጉጉሞ  ወዘተ የተባሉ ነገዶች ስለመኖራቸው የሚዘግቡ አፈታሪኮች ስላሉ፤ የእነዚህ ህዝቦች ታሪክ በኢሮብ ህዝብ ታሪክ ላይ ያለው እንድምታ ምን ሊሆን ይችላል? በኢሮብ ምድር፣ በተለያዩ ቦታ የሚገኙ ካራንሓሲት / አጀብ ባሉ የድጋይ ክምርና አፈር ድብዳብ በአከባቢው ካለው መሬት ተለይቶና ከፍ ብሎ የሚገኝ፣ በውል መቃብር ይሁን ወይስ የቤት ቁሳቁስ ወዘተ የተቀበረበት መሆኑ የማይታወቅ፤ በቦተው ላይ ለብዙ ዓመታት የዘለቁ ነገሮች/ የሚሰጡት የታሪክ ምስክርነተስ ምን ሊሆን እንደሚችል እንዴት መገመት ይቻላል?

ለዚህ ሁሉ ዓይነተኛ መልስ ሊሆን የሚችለው ዋነኛው ፍሬ ሃሳብ፣ በአቶ ሚካኤል ገብራይና በአቶ ጊደይ ሃጎስ (ዑንዱዐ) የኢሮብ ታሪክ አዘጋገብ ላይ በመሞረከዝ፤ ከብዙ ዓመታት በፊትና በቅርቡ ዓመታትምኳ ቢሆን፣ ዓጋመ፣ የእነ ወልዱ እና የእነደጊያት ሱባጋድስ መናሃርያ በነበረበት ጊዜ በአከባቢው ይንጸባረቅ የነበረው ሂደት በዓይነ ሂሊናችን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት፡ የሴም ነግዶች ቋንቋና ባህል አከባቢውን ሲገዛ በቆየው የኢሮብ ወይም የሳሆ ባህልና ቋንቋ ላይ የበላይነቱን ይዞ እየዋጠው መሄዱን ነው። ለዚህም እንደምስክርነት ሊሆን የሚችለው፣ ለምሳሌ፣ ዝነኛው ደግያት ሱባጋድስ፣ ከኢሮብ የሓሳባላዓረ ልጅና የኢሮብ ቋንቃ ወይም ሳሆ ተናጋሪ ሆነው፤ ትግሪኛ ተነጋሪ ኢሮብ/ሳሆን እና ትግሪኛ የማይናገረው ኢሮብ/ሳሆንም ጭምር ባንድነት ሲያስተዳድሩ መኖራቸውን ነው። ከዚህም በተጨማሪ በደጊያት ሱባጋድስ ግዛት፤ ብላታን ጌታ ሆነው ያስተዳድሩ የነበሩት ታዋቂው ብላታ ፉሱሕ ወልደጊዮርግስ የአድጋዲዓረ ተወላጅ፣ ኢሮብ መኖራቸውን ነው።

ስለሆነም፤ ለማጠቃለል ያህል፤ በእኔ እምነት፣ አቶ ሚካኤል ገብራይና አቶ ጊደይ ዑንዱዐ እንዳሉት ሁሉ፣ ኢሮብ/ሳሆ ተናጋሪ በዓጋመና አከባቢው ከጥንት የኖረ ህዝብ ሲሆን፤ በዝህ ህዝብ ላይ የተካሄደው ዘገምተኛ ለውጥ ቢኖር፤ የህዝቡ የድሮ ቋንቋና ባህል በኢኮኖሚ የበላይነቱን በያዘው በሴም ቋንቋና ባህል እየተዋጠ መሄዱንና ነባሩን የኢሮብ/የሳሆ/ ቋንቋ እየተዳከመና የነበረውን መሪ ቦታ እያጣ ማዝገምን ነው። ከጊዜ በኋላም፣ አሁን ወደምንገኝበትና የኢሮብ/ሳሆ/ ተናገሪ አናሳ ብሄረሰብ ወደ ሆነበት ደረጃ ተደረሰ። በዚሁ አካሄድ ከቀጠለ ደግሞ ጭራሽ የኢሮብ ብሄረስብ ወደሚጠፋበት ደረጃ ሊደረስ እንደሚችል የሚያመላክት እውነታ እንዳለ ይስተዋላል።

ስለሆነም መንግሰትና የኢሮብ ህዝብ በአፋጣኝ ለዚህ አሳሳቢ የኢሮብ ብሄረሰብ የህልውና ጥያቄ አስቸኳይና አጣዳፊ እርምጃ ቢወስዱ በኢሮብ ህዝብ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንደሚኖራቸው አያጠራጥርም። ለዚህ ለተቀደሰ አላማ ዋና መንደርደርያ ሊሆኑ ከሚችሉ ቀዳሚ ክንውኖች ውስጥ፤

1.   በኢሮብ ምድር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሁሉ ኢሮብኛ /የሳሆ/ ቋንቋ እንደመደበኛ ትምህርት እንዲሰጥ ቢደረግና ለዚሁ የሚሆን የትምህርት መገልገያ ቁሳቁስ በአስቸኳይ እንዲዘጋጅ ቢደረግ፤

2.   በኢሮብ ምድር በሚገኙ በአንደኛና በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህረት ቤት የሚሰጠው መደበኛ ትምህርት በኢሮብኛ /የሳሆ/ ቋንቋ እንዲሰጥ ቢደረግና ለዚሁ የሚሆን የትምህርት መገልገያ ቀሳቁስ በአስቸኳይ እንዲዘጋጅ ተደርጎ መርሃ ግብሩም በአፋጣኝ በተግባር እንድውል ቢደረግ፤

3.   ማንኛውም በኢሮብ ብሄረሰብ ውስጥ የሚከናወን የአስተዳደር ተግባር ሁሉ በኢሮብኛ /በሳሆ/ ቋንቋ እንዲከናወን በጥብቅ ቢሠራበት፡፡

4.   ከዚህ ቀደም እነ አባ አብርሃም ሀይሉ ያሉበት ኮሚቴ እንዳቀረበው ገንቢ ሃሳብ ሁሉ የኢሮብ ህዝብ የመሰረታዊ ትምህርትና የዜና ሽፋን የሚያገኝበት በቋንቋው የሚተላለፍ የሬድዮ ፕሮግራም ስርጭት ቢተገበር መልካም ጅምር እንደሚሆን የብዙሃኑ የኢሮብ ተወላጆች ስምምነት እንደሆነ እምነቴ ነው።     

ማገናዘቢያ (References)

1)     አባ ተስፋይ መድህን፤ 1993፤ ታሪኽ ኢሮብ/ ሓጺር መግለጺ/ ዓዲግራት

2)     መምህር በርሀ ዝግታ፤ 2000፤ መበቖልን ታሪኽን ህዝቢ ኢሮብ


ኃይለስላሴ ዮሓንስ (ሞደይሳ) 

ይህ የኢሮብ ታሪክ ጥያቄዎችና ኣባባሎች በሚል ርእስ የቀረበው መጣጥፍ ክዚህ በፊት በ“ኢሮብ ማብሎ” ድረ-ገጽ ላይ በሶስት ክፍሎች ተመድቦ ወጥቶ ነበር። ፅሑፉ ስለ ኢሮብ ታሪክ መመራመር ለሚፈልጉት ኣሁንም ጠቃሚ ሆኖ ስለታየኝ በዚሁ በኢሮብ ኣድቮካሲ ድረ-ገጽ ላይ እንደገና ተለጥፏል። የቀሩት ሁለት ክፍሎች ቀጥሎ ይለጠፋሉ።

ግርማይ ተስፋገርጊስ


የኢሮብ ታሪክ ጥያቄዎችና ኣባባሎች-ክፍል ፩

Copy of የኢሮብ ህዝብ ኣፈታሪክ_1.pdf
የኢሮብ ህዝብ ኣፈታሪክ የታረመ የተሻሻለ-1-1-1-1.pptx

የኢሮብ ታሪክ ጥያቄዎችና ኣባባሎች-ክፍል ፪

የኢሮብ ታሪክ ጥያቄዎችና ኣባባሎች ክፍል ሁለት.pdf

የኢሮብ ታሪክ ጥያቄዎችና ኣባባሎች-ክፍል ፫

የኢሮብ ህዝብ ታሪክ ክፍል ሶስት.pdf

Documentary on Irob History

Irob Political Figures in Modern Ethiopia

ተስፋዬ ደበሳይ- አንጋፋው ኢህአፓ

Remembering Dr Tesfay Debesay.pdf

Emperor Yohannes IV

Media Highlights About Emperor Yohannes IV

ታሪክ ለባለ ታሪኩ

Tarik-le-Bale-Tariku_ዮህንስ 4ኛdf.pdf

Wiki References about Emperor Yohannes IV

Yohannes IV - Wikipedia.pdf
Ethiopian–Egyptian War - Wikipedia.pdf
British Expedition to Abyssinia - Wikipedia.pdf