ኦሮባ (WELCOME)
ኢሮብ ማለት/ስንል
ABOUT IROB PEOPLE
ኢሮብ በአሁኗ ትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምስራቅ የምትገኝ ወረዳ ናት ። የኢሮብ ማዕከልና ለረጅም ዓመታት ዋና ከተማ የነበረችው 'ዓሊቴና' ከክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ 155 ኪሜ የምስራቃዊ ዞባ ዋና ከተማ ከሆነችው ዓዲግራት ደግሞ 45 ኪሜ ርቀት ላይ ትገኛለች ። ኢሮብ ላለፉት 28 ዓመታት "በልዩ ወረዳነት" ስትመደብ የወቅቱ ዋና ከተማ ደግሞ "ዳውሓን" ትባላለች ። ዳውሓን'ም ለዓሊቴና ቅርብ ስለሆነች ከዓዲግራት ተመሳሳይ ርቀት ላይ ትገኛለች ። እጅግ አነስተኛ በሆነ የመሬት ስፋት ላይ ያረፈችው 'ዳውሓን' የወደፊት ዕድገት የተወሰነ እንደሚሆን ከወዲሁ ይገመታል ።
የኢሮብ የመሬት መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ/ቶፖግራፊ/ እጅግ ተራራማና ቀጥ ባሉ ሸንተረሮችና ጥልቅ (deep) ሸለቆዎች የተሞላ ነው ። በዚህም የተነሳ ታራሽ መሬቱ እጅግ አነስተኛ ሲሆን ፣ ከአጠቃላይ ይዞታው ከ1% እንደማይበልጥ የሚጠቁሙ ጥናቶች አሉ። የአከባቢው የአየር ሁኔታ ደረቃማ(arid) ሲሆን ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም አነስተኛ የሚባል ነው።
ኢሮብ፣- በምዕራብ አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪ ሕዝቦች ጋር የምትዋሰን ሲሆን፣ ይህንን ምዕራባዊ መስመር ይዘን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ስንጓዝ ኢሮብ በጉሉማክዳ ወረዳ ስትዋሰን፣ ቀሪው ደግሞ በኤርትራው የአካለ-ጉዛይ ትግርኛ ተናጋሪ አጎራባች ሕዝብ ትዋሰናለች። ቀጥሎ ያለው ሰሜናዊ ጫፍ ደግም ከአምባ ሶይራና ማኮ ከሚባሉ የኤርትራ የመሬት ይዞታ እና ሴሚናዊ የኢሮብ ጫፍ የመሬት ይዞታ መኻል ሰንጥቆ ወደ ዒንደሊ በሚወርደው ወንዝ ትዋሰናለች። አሁንም ይህን ወንዝ ሳንለቅ ተከትለን ከሰሜን ጫፍ የምስራቁን አቅጣጫ ይዘን ወደ ደቡባዊ ጫፍ እስክንደርስ ደግሞ በኤርትራዊያን የሳሆ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ጋር ትዋሰናለች። ዙረን ወደ ደቡባዊው ጫፍ ስንመለስ ደግሞ በዓፋር ክልልና ከሳዕሲዕ-ፃዕዳእምባ ወረዳ ጋር ትዋሰናለች።
የኢሮብ ምስራቃዊ ወሰን ራንዳ-ኮማ እና ራጋይሊ ድረስ ስለሚዘልቅ እስከ ቀይ ባሕር የሚተርፈው የየብስ ርቀት ሩቅ ኣይደለም።
በሌላ አነጋገር ከየትኛውም የትግራይ መሬት እንደ ኢሮብ ለቀይ ባሕር የቀረበ ቦታ የለም። የኢሮብ ሕዝብ ከነዚህ አጎራባች ሕዝቦች በሰላም በመከባበርና በፍጹም መግባባት የኖረና የሚኖር ሕዝብ ነው። ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ ትስስሩም የተሳሰረና የተጋመደ ነው። "ኢሮብ' ሲባል የማሕበረሰቡና የወረዳው የጋራ ስያሜ የሚወክል ሲሆን፣ ወረዳ = ኢሮብ ፣ ማሕበረሰብ = ኢሮብ ፣ በመባል ይታወቃል። ቋንቋውም 'ሳሆ' ይባላል። የኢሮብ ሕዝብ የራሱ ወግ፣ ባህልና እሴቶች እንዲሁም የራሱ የሆነ የፓለቲካ-እሳቤና የግንባታ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው። አዋሳኝ ትግርኛ ተናጋሪ ሕዝቦች አከባቢውን "ዓዲ-ኢሮብ” በማለት ሲጠሩት ነዋሪውን ደግሞ "ሕዝቢ-ኢሮብ" ይሉታል። ሳሆ ተናጋሪዎች ሕዝቡን 'ኢሮብ' መሬቱን ደግሞ 'ኢሮብ-ዲክ/ኢሮብ-ባዶ' በማለት ሲጠሩት፣ የሁለትዮሽ ማሕበራዊ ትስስሩን "ኢሮብከ-ሓዶ"፣ በሚል ሲገልጹት ኢሮቦችም በተመሳሳይ ሓዶከ-ኢሮብ በማለት የተለየ ቅርበትና ሚዛን ይሰጡታል።
የኢሮብ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሲሆን እጅግ አነስተኛ መጠን ያላቸው የእስልምና ተከታይ ነዋሪዎችም ይገኛሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አብዛኞቹ ሰዎች የኢሮብ ሕዝብ የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ብቻ እንደሆነ ይገምታሉ። ግምቱ ግን የግንዛቤ ክፍተት ከመሆኑ ውጭ መሬት ላይ ያለ ሃቅ አይወክልም። ይልቁንም ከኢሮብ ሕዝብ የካቶሊክ ተከታዩ 1/3ኛ ገደማ ብቻ ሲሆን አብላጫው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው። የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኣከባቢዉ ከሁሉም የቀደመ ረጂም ዕድሜ አለው። በመቀጠል ደግሞ ኢሮብ ህዝብ የደቂቀ ኢስጢፋኖስ ተከታዮችን በመቀበልና በማስተናድ ይታወቃል። ሁለቱንም፣ ማለት የቆየው የኦርቶዶክስ-ተዋህዶ እምነት ተከታዮችንና ደቂቀ ኢስጢፋኖስችን ጎን ለጎን አስተናግዷል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ዝነኛው የጉንዳጉንደ ገዳም የሚገኘው በኢሮብ ወረዳ ሲሆን፤ ለግዞተኞች የደቂቀ ኢስጢፋኖስ መነኮሳት መጠግያ እንዲሆናቸው የኢሮብ ህዝብን በማስተባበር ጉንዳጉንዴን ያስገነባው ቡራሱባጋዲስ የሚባሉ የሓሳባላ-ኢሮብ ተወላጅ ናቸው። ገዳሟ የተገነባችው ዓሲምባ ተራራ ግርጌ ስር ካለው ሰዋራ ቦታ ሲሆን፤ ሽሽት ላይ ለነበሩ መነኮሳት እጅግ አመቺ ሆናላቸዋለች። የደጃች ሱባጋዲስ አስከሬንም በኑዛዜያቸው መሠረት ወደ ትውልድ ቦታቸው እንዲመለስ ሆኖ በዚችው ገዳም ተቀብሯል። ኣሁንም የደጃች ሱባጋዲስ አስከሬንና የሁለት ልጆቻቸው (የደጃች ወልደሚካኤልና የደጃች ሓጎስ) ሬሳዎች የያዙ ሳጥኖች በገዳሙ ቅጥር ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ።
በተመሳሳይ በሰሜኑ ያገራችን ክፍል የካቶሊክ እምነትን ተቀብሎ በማስተናገድ አሁንም የኢሮብ ሕዝብ ቀዳሚ ነው። ቀጥሎም መነሻውን ዓሊቴና በማድረግ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ተስፋፍቶ ኤርትራን ቀጥሎም ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎችን እንደአዳረሰ ይታወቃል።
የኢሮብ ሕዝብ እንግዳን በመቀበልና በማቀብ የሚመስለው የለም። ኢሮቦች ዘንድ ሰውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ሽምጋይም ሽምግልናም የማይገኝለት ክሕደት ነው። ከዚህ ጥፋት ውጭ ሽማግሌና ሽምግልና የማይፈታው ወንጀል የለም።
ሌላውና የኢሮብ ሕዝብ አስመልክቶ ብዙዎችን ሲያወዛግብ የሚታየው ጉዳይ ቢኖር የኢሮብ ሕዝብ ልክ እንደ ዓፋርና ኩናማ በኤርትራና በኢትዮጲያ ውስጥ ይካለላል ወይም ይኖራል የሚል ሲሆን፣ መልሱ ግን አጭርና ግልፅ ሆኖ የኢሮብ ሕዝብ የሚገኘው ኢትዮጲያ ትግራይ ውስጥ ብቻ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን የኢሮብ ሕዝብ በመዋዕሉ ኤርትራ ውስጥ የተካለለበት ወይም የተዳደረበት አንዳች ወቅት አልነበረም፣ ኖሮም አያውቅም። እንዲያውም እንደ እውነቱ ከሆነ ዘመናዊ የአከላለል ስርዓት ተጀምሮ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በራሱ አካባቢና የአስተዳደር ስርዓት፣ ማንነቱን ጠብቆ የኖረ ሕዝብ ነው። የራሱ ሕግጋት በማርቀቅ ልክ እንደ ዘመኑ ቃለ ጉባኤ ያዥ በመሰየምና በየርዕሱ የሚይዙ ሰዎች በመሰየም በሕግ አግባብ ሲተዳደር ነበር። (ለምሳሌ፤ ቃለጉባኤ ለመያዝ የተለየ የማስታወስ ተሰጥዎ ያላቸው ሶሰት ሰዎች የሚመረጡ ሲሆን የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ብዥታ ሲፈጠር እነዚህ ሰዎች ይጠሩ ነበር ይባላል) ይህ ብቻ ሳይሆን በአግባቡ ስላልተሰነደ ነው እንጂ ሌላውን የአከባቢ ሕዝቦችን ከዘመናዊ ሕግጋት ጋር ያስተዋወቀ ሕዝብ ነው።
አሁንም ከኢሮብ ጋር ተያይዞ መረሳት የሌለበት ሌላ ጉዳይ ቢኖር የትምህርት ጉዳይ ነው። ይኸውም መደበኛ ትምህርት ኢሮብ ዓሊቴና ውስጥ የተጀመረው በ1830ዎቹ መጨረሻ አከባቢ ሆኖ ይህም በሀገሪቱ ደረጃ ቀዳሚ ያደርገዋል። ለዚህ ደግሞ የካቶሊክ ቤተ/ያን ግዙፍ አስተዋጽኦ የሚረሳ አይደለም።
ኢሮብ አድቮካሲ አሶሴሽን ታሕሣሥ 01/2015
Though the website contains general information about Irob in many sections, we thought providing a brief introduction about Irob from the outset could be helpful.
----
By Sauba Hais
Irob is one of the Ethiopian territories invaded by the Eritrean armed forces this year. When news of the invasion broke, I observed that many Ethiopians, including Tigrayans, did not know anything about Irob, even its existence. After almost five months, there is not much change in this regard. The aim of this paper, therefore, is to provide some information about the people and the location. It will also discuss the current condition of the people after the invasion.
LOCATION, LANGUAGE AND RELIGION
The Irob people occupy a small, semi-arid, mountainous region with a wide altitudinal range in which almost all types of crops can be potentially cultivated. It is located in Agame, northeast Tigray/Ethiopia. The territory is bordered by the Endeli River to the east and to the north-east, by Shumezana to the north-west, by Guolomakeda to the west, Sae`se` to the south and Afar Region to the south-east. The Irob neighbors to the east and north-east are predominantly Muslims and speak the Saho language. The Afars are Muslims as well and, of course, they speak the Afar language which is very similar to the Saho language. The other neighbors are Tigrigna speaking Christian highlanders.
The Irobs who live in this geographic location speak Saho. Many other Irob descendants who live in the rest of Agame and some other adjacent places have adopted the Tigrigna language. Irob is an ethnic community made up of three sub-groups: Adgadi-ârere, Bouknaiyti-âre and Hasaballa. Adgadi-âre and Hasaballa are predominantly Tewahido Christians, while Buknaiyti-âre is mostly Catholic.
BACKGROUND
Most of the three Irob groups claim to be descendants of one man, Summe. Acccording to the oral history of the people and several written records, Summe’s father, Negus (King) Werede-Mehret, is believed to have come from Tsira'e in Kilite-Awla'elo, Tigray about 800 years ago. That is around the time when the so-called “Salomonic” dynasty took control of political power of the Ethiopian empire from the Zagwe dynasty. It is recounted that WoredeMehret, himself a local king, was a descendant of Emperor Yitbarek of the Zagwe dynasty. Negus WeredeMehret’s forefathers left their ancestral land probably for political reasons related to the change of political power in Ethiopia. In fact, for many centuries, the Irobs isolated themselves to this remote, militarily strategic, mountainous region keeping their distance from the political centers.
Many different tribes inhabited the Irobland before the descendants of Weredemehret went there. But most of those tribes left the region for good. The main ethnic group who dwelled in the region when the descendants of Weredemehret moved there were the Kayayta people. Today too the Kayayta people are one of the main social groups who live in the Irobland. The Aydola (Aydoli-dik) are some of the early inhabitants of the region as well. Anyway it is not the purpose of this article to deal with the question of the Irob ethnic group in general. However, putting it briefly the Irob ethnic group is a community composed of the descendants of Kayayta, Summe, Aydola, Ga’aso, Dabrimela, Hado/Hazo and some few members of other lineages. Continue reading the entire article here article